Konso News artwork

Konso News

343 episodes - Tigrinya - Latest episode: 8 months ago -

It presents daily news digests about Konso people and its administration, politics, social issues, culture, and development efforts.

News
Homepage Apple Podcasts Google Podcasts Overcast Castro Pocket Casts RSS feed

Episodes

344 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

September 01, 2023 10:48 - 13 minutes - 12 MB

የዕለተ ዓርብ ነሐሴ 26  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) 3ኛው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ በካራት ከተማ እየተካሄደ ነው 2) በቅርቡ የተመሠረተው አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላቱን ዝርዝር ይፋ አደረገ 3) የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ ተነገረ

343 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

August 04, 2023 16:36 - 11 minutes - 11.1 MB

የዕለተ ዓርብ ሐምሌ 28  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) በኮንሶ ዞን የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ 2) የካራት ከተማ ተሽከርካሪ ባለንብረቶችና የግል ማህበራት እየተገነባ ያለውን የካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ማዕከል ጎበኙ 3) የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከሥርቆትና ከኩረጃ ነጻ ሆኖ መጠናቀቁን ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ 4)   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ በግልጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

342 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

July 28, 2023 17:18 - 8 minutes - 7.73 MB

የዕለተ ዓርብ ሐምሌ 21  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) በኮንሶ ዞን የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የዚህ አመት የዕቅድ አፈጻጸሞችና የመጪውን አመት ዕቅዶች ግምገማ ማካሄዳቸው ተገለጸ 2) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን የአቶሚክ ኢነርጂ ትብብር ፍኖተ ካርታ እንደሚፈራረሙ ገለጹ 3) ሦስት ሺህ ተሽከርካሪዎችን ጭና በመጓዝ ላይ የነበረች መርከብ መቃጠሏ ተገለጸ

341 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

July 21, 2023 12:33 - 16 minutes - 14.9 MB

የዕለተ ዓርብ ሐምሌ 14  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮንሶ ልማት ማህበር አባል ተቋም ሆነ 2) የኮንሶ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ለዩንቬርስቲ መግቢያ ፈተና መዘጋጀታቸው ተገለጸ 3) የመውጫ ፈተና ላላለፉ ተማሪዎች ዲግሪ የሚሰጡ ተቋማት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ 4) የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ዕጩዎች ሲቀርቡ ምክክር እንዲደረግ ጥያቄ አቀረበ

340 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

July 14, 2023 17:29 - 13 minutes - 12.9 MB

የዕለተ ዓርብ ሐምሌ 7  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) በአባላት ድጋፍ የተጀመረው የድንገተኛ ህክምና ማዕከል ግንባታ እንዲፋጠን አባላት እንዲረባረቡ የኮንሶ ልማት ማህበር ጥሪ አቀረበ 2) የአካባቢ ምርጫን በቀጣዩ ዓመት ለማካሄድ፤ በጀትን ጨምሮ ሌሎች “አስፈላጊ ነገሮች” መመቻቸት እንዳለባቸው ምርጫ ቦርድ ገለጸ  3) ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአራት ወራት ውስጥ ወደ ስምምነት ለመምጣት ተስማሙ 4) ዛንዚባር ጸጉራቸውን ሽሩባ በሚሰሩ ወንዶች ላይ እገዳ ጣለች

339 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

July 07, 2023 09:18 - 11 minutes - 10.3 MB

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 30  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮንሶ ዞን ጉብኝት አደረጉ 2) የፌዴሬሽን ምክር ቤት “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” በሚል ስያሜ አዲስ ክልል እንዲደራጅ ውሳኔ አሳለፈ 3) ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ “ሀገሪቱ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ እያመራች ነው”’ መባሉን ውድቅ አደረጉ 4) በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት ዋይት ሃውስ ኮኬይን አደንዛዥ እጽ ተገኘ

338 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

June 30, 2023 18:58 - 12 minutes - 11.5 MB

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) የኮንሶ ባህል ፌስትቫ ክብረ በዓል መጀመሩ ተገለጸ 2) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሰብሳቢዋ ድንገተኛ ስንብት በተለያየ ስሜት እንደተቀበሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተናገሩ 3) አሜሪካ ኢትዮጵያን ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ሰረዘች

337 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

June 23, 2023 14:21 - 16 minutes - 15 MB

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ ክልላዊና ብሔራዊ ፈተና ስለሚወስዱ ተማሪዎች መረጃ ሰጠ 2) የኮንሶ ባህል ፌስቲቫል ሰኔ 23 ሊጀመር ነው 3) በወላይታ ሕዝበ ውሳኔ ባዶ መታወቂያ እየሞላ ለመራጮች ሲያድል የነበረ ግለሰብ መያዙ ተገለጸ 4) የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ግንኙነት በፓርቲ መስመር እንዳይደፈጠጥ ትኩረት እንዲደረግ ተጠየቀ 5) ኢትዮጵያ አበዳሪ ተቋማት ቃላቸውን እንዲያከብሩ ጠየቀች

336 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

June 16, 2023 18:49 - 16 minutes - 15.3 MB

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 9  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) አጫጭር ሳምንታዊ ኮንሶ ነክ ዜናዎች 2) በሕገ መንግሥቱ ላይ የታሰበው ማሻሻያ በገለልተኛ ተቋማት እንዲመራ ተጠየቀ 3) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው “የባሎች ትምህርት ቤት” ተከፈተ

335 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

June 09, 2023 09:58 - 13 minutes - 12.1 MB

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 2  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ 3) በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የምግብ ዕርዳታ እንዲጀምር አቶ ጌታቸው ጥያቄ አቀረቡ 4) ናይጀሪያ የዩንቨርሲቲ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ጾታዊ ግንኙት እንዳይጀምሩ የሚከለክል ህግ አወጣች

334 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

June 02, 2023 12:17 - 13 minutes - 12.3 MB

የዕለተ ዓርብ ግንቦት 25  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) ብልጽግና ፓርቲ “ፍላጎታቸውን በኃይል ለማሳካት የሚጥሩ ጽንፈኛ” አካላት “በእጅጉ ፈትነውኛል” አለ  3) በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት ዙሪያ ለመነጋገር የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው ተባለ 4) አሜሪካ ከሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ባላቸው ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች

333 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

May 26, 2023 10:50 - 16 minutes - 14.8 MB

የዕለተ ዓርብ ግንቦት 18  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) የትምህርት ማስረጃቸው እንዲጣራ ከተደረገባቸው 225 ሠራተኞች ውስጥ 40 በመቶዎቹ ሕገወጥ መሆናቸው ተገለጸ 3)  ዩኒቨርሲቲዎች በዋጋ ግሽበት ምክንያት ተማሪዎቻቸውን መመገብ በማይችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸው ተነገረ 4)  የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪ በደቡብ አፍሪካ ተያዙ  

332 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

May 19, 2023 10:45 - 13 minutes - 12.4 MB

የዕለተ ዓርብ ግንቦት 11  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) የሕዝብና ቤት ቆጠራ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ይካሄዳል ተባለ 3) ሕወሓት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረበ

331 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

May 12, 2023 09:14 - 14 minutes - 13.6 MB

የዕለተ ዓርብ ግንቦት 04  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሦስት የቁጫ ፓርቲ አባላትን አባረረ 3) ነዳጅ ማደያዎችን የሚቆጣጠር አዲስ ቴክኖሎጂ በሥራ ላይ ሊውል ነው ተባለ 4) የሮኬት ጥቃት የደረሰባት እስራኤል ከፍተኛ የጋዛ የጦር አዛዥ መግደሏን አስታወቀች

330 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

May 05, 2023 09:32 - 14 minutes - 13.5 MB

የዕለተ ዓርብ ሚያዝያ 27  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) ኦነግ ሸኔና መንግስት በታንዛኒያ እያደረጉ የነበረው የሰላም ውይይት ያለስምምነት ተጠናቀቀ 3) በአማራ ክልል መከላከያ ሰራዊትና ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ 4) በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን ሩሲያ አስታወቀች

329 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

April 28, 2023 09:35 - 10 minutes - 9.47 MB

የዕለተ ዓርብ ሚያዝያ 20  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ ኮንሶን የሚመለከቱ አጫጭር ዜናዎች 2) በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት 11 ሰዎች ተገደሉ 3) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ መገደላቸው ተገለጸ 4) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦርነቱ ውስጥ ከገቡት  የሱዳን ጀነራሎች ጋር መወያየታቸውን ገለጹ

328 || ኮንሶ ዜና || የኮንሶ ዜና ሚድያ ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News || Konso News Weekly News Digest

April 21, 2023 08:21 - 14 minutes - 13 MB

የዕለተ ዓርብ ሚያዝያ 13  ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡ 1) ሳምንታዊ አጫጭር ኮንሶ ነክ ዜናዎች 2) በኮንሶ ዞን በዓይነቱ ልዩ የሆነ የመምህራን ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ 3) በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጎጂዎች የካሳ ፈንድ እንዲቋቋም ተጠየቀ 4) በሱዳን በተቀሰቀሰ ጦርነት ከ300 በላይ ንጹሃን ተገደሉ

327 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

January 09, 2023 15:39 - 13 minutes - 12.2 MB

የዕለተ ሰኞ ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ ከጸጥታ ችግሮች ነጻ እንዲሆን የዞኑ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ ኢትዮጵያ በትክክለኛ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሕገ መንግሥት ማበጀት እንደሚገባት ማሳሰቢያ ተሰጠ በአንድ ጊዜ ቻርጅ 1000 ኪ.ሜ የሚጓዝ መኪና በአውስትራሊያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሠራቱ ተገለጸ

326 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

January 04, 2023 10:04 - 10 minutes - 9.74 MB

የዕለተ ረቡዕ ታህሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን በሚገኙ የመካነ ኢየሱስና የአካለ ኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የአንድነትና የሰላም ኮንፍራንስ ተካሄደ 2. ሕወሓትን ትጥቅ የማስፈታት ሒደት ሲጠናቀቅ የሽብርተኝነት ፍረጃው ተነስቶ ክስ እንደሚቋረጥ ተነገረ 3. በሴኔጋል ነፍሰጡር የፓርላማ አባልን በጥፊ የመታው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

325 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 29, 2022 17:56 - 8 minutes - 8.32 MB

የዕለተ ሐሙስ ታህሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የመንግስትና የህወሓትን የሰላም ስምምነት የሚቆጣጠርና የሚያስከብር የተልዕኮ ቡድን መቋቋሙ ተገለጸ 2. በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማና መዝሙር ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮች በህግና ፖሊሲ መሠረት እንዲፈቱ ኢሰመኮ አሳሰበ 3. የኮሮና ቫይረስ የመራባት ሂደትን የሚገታ አዲስ መድሃኒት መሠራቱ ተገለጸ

324 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 27, 2022 17:52 - 9 minutes - 8.76 MB

የዕለተ ማክሰኞ ታህሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ነው 2. የመከላከያ ሰራዊት በመቀሌ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ስራውን በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ተገለጸ 3. አሜሪካ እና ኔቶ ሩሲያን ለማጥፋት በዩክሬን የጦር ሜዳ ላይ ድልን መቀዳጀት ይፈልጋሉ ተባለ

323 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 23, 2022 08:49 - 11 minutes - 10.6 MB

የዕለተ ዓርብ ታህሣሥ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆጣጠሪያ መሥመር ተመርቆ መከፈቱ ተገለጸ 2. የፌደራል መንግስትና የህወሓት አመራሮች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቀሌ ላይ ተገናኝተው ይመክራሉ ተባለ 3. በእስራኤል የተሠራው በራሪ ተሽከርካሪ የበረራ ሙከራ አደረገ

322 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 21, 2022 11:22 - 9 minutes - 8.96 MB

የዕለተ ረቡዕ ታህሣሥ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር በቀጠናዊ ሰላምና አንድነት ዙሪያ ውይይት መካሄዱ ተገለጸ 2. በኮንሶ ዞን ለአዲሱ “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው 3. ብሪታንያ ገንዘቧን ቀየረች

321 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 19, 2022 10:21 - 10 minutes - 9.52 MB

የዕለተ ሰኞ ታህሣሥ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን የሥራ ዕድል ፈጠራና እንተርፕራይዞች መምሪያ ከ10 ሺህ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን መለቱን አስታወቀ 2. የፌደራሉ መንግስት በአዲስ አበባ ባሉ ትምህርት ቤቶች የኦሮምያን  ባንዲራ ለማውለብለብና መዝሙር እንዲዘመር የሚደረገው ግፊት እንዲቆም የፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ መሰጠቱ ተገለጸ 3. አርጀንቲና ከ36 አመታት በኋላ ለ3ኛ ጊዜ የዓለምን ዋንጫ አነሳች

320 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 14, 2022 18:17 - 10 minutes - 9.9 MB

የዕለተ ረቡዕ ታህሣሥ 05 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በምግብ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት በመፈጸም ለንጹሃን ሞት ምክንያት በሆኑ ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ ተበየነ 2. ፌስቡክ ኩባንያ በኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ክስ ተመሠረበት 3. ኤክቶላይፍ የተሰኘና በአመት 30 ሺህ ህጻናትን በሰው ሰራሽ ማህጸን የሚያመርት ኩባንያ በጀርመን አገር መከፈቱ ተገለጸ

319 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 12, 2022 17:18 - 12 minutes - 11.7 MB

የዕለተ ሰኞ ታህሣሥ 03 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ መካከል የዕርቀ ሰላም ኮንፍረንስ ተካሄደ 2. የብልፅግና ፓርቲተወካይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ ጠራ 3. አሜሪካ የቀዝቃዛው የዓለም ጦርነትን ስህተት በአፍሪካ እንደማትደግም አስታወቀች

318 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 08, 2022 10:09 - 11 minutes - 11.1 MB

የዕለተ ሐሙስ ህዳር 29  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው 2. በኦሮሚያ ክልል ግጭቶችና ጥቃቶች የሚከሰቱባቸው ቦታዎች መጨመራቸውን ኢሰመኮ ገለጸ 3. ወንድ ልጅን መጸነስ የሚያስችለው የዋይ ክሮሞዞም በመጥፋት ላይ መሆኑን ሳይንቲስቶች ተናገሩ

317 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 05, 2022 10:14 - 13 minutes - 12.5 MB

የዕለተ ስኞ ህዳር 26  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ የተሰኘ ድርጅት በካራት ከተማ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ 2. በኮንሶና በዲራሼ ህዝቦች መካከል የተከሰተውን አለመግባባት ለመፍታት የሰላም ኮንፍረስን ተካሄደ 3. በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው 4. ኢንዶኔዥያ ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነትን በወንጀልነት የሚቀጣ ህግ ልታጸድቅ ነው

316 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

December 01, 2022 17:09 - 14 minutes - 13.5 MB

የዕለተ ሐሙስ ህዳር 22  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው ሥራ ላላገኙ ወጣቶች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ 2. የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ መጻሕፍትን ለማሳተም 29 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ 3. መንግስት "የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዕቅድ በተመለከተ ምክክር እየተደረገ ነው” አለ 4. ናይጀሪያ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትእንዳይሰጡ አገደች

315 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

November 24, 2022 10:53 - 13 minutes - 12.1 MB

የዕለተ ሐሙስ ህዳር 15  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በአምቡላንስ ከባድ የጦር መሣሪያ ሲያዘዋዉሩ የተያዙ ግለሰቦች በእሥራት ተቀጡ 2. የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት፤ በመጪው ቅዳሜ ሊያከብር ነው 3. በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት የተካተተበት አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

314 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

November 23, 2022 11:10 - 11 minutes - 10.3 MB

የዕለተ ረቡዕ ህዳር 14  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ለአሽከርካሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና መሰጠቱ ተገለጸ 2. በታጠቁ ኃይሎች በኩሱሜ ብሔረሰብ ላይ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰ ነው 3. በስምምነቱ አተገባበር ጉዳይ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ 4. ቱርክ በከባድ ርዕደ መሬት ተናጠች

313 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

November 21, 2022 10:57 - 8 minutes - 7.66 MB

የዕለተ ሰኞ ህዳር 12  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ልማት ማህበር ከጂ አይ ዚ ባገኘው ድጋፍ በአማሮ ልዩ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መሥራቱን አስታወቀ 2. በኮንሶ ዞን የመብራት ችግር በባንኮች ላይ የንብረት ውድመትና ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑ ተገለጸ 3. የግብጽ እና ቱርክ መሪዎች ከአስርት አመታት ውጥረት በኋላ በዓለም ዋንጫ ተጨባበጡ

312 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

November 17, 2022 17:32 - 13 minutes - 12.4 MB

የዕለተ ሐሙስ ህዳር 8  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ 2. ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሌብነትከኢትዮጵያ የጸጥታ ሥጋቶች እኩል እንቅፋት መሆኑን ገለጹ 3. ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ ጀመረች 4. የዓለም ህዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን መድረሱ ተገለጸ

311 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

November 16, 2022 17:20 - 17 minutes - 15.8 MB

የዕለተ ረቡዕ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ልማት ማህበር ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ግንባታ ለማከናወን እያቀደ መሆኑን አስታወቀ 2. በኮንሶ ዞን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው 3. ሀገር መከላከያ በትግራይ ክልል ለሚያካሂዳቸው ሥራዎች የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ 4. በአንድ ወቅት ከኦባማ ጋር የደነሱት አዛውንት ሴት በ113 አመታቸው አረፉ 5. የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ከ50 በመቶ በላይ መቀነሱ ተገለጸ

310 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

November 14, 2022 18:14 - 10 minutes - 9.42 MB

የዕለተ ሰኞ ህዳር 5  ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ቀደም ሲል ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮችና ድርቅ ምክንያት ከተጎዱ ወገኖች 84 በመቶ ያህሉ እርዳታ ማግኘታቸውን የዞኑ መንግሥት አስታወቀ 2. በመጭበርበሩ ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ነገ ይወጣል ተባለ 3. የሃይማኖት ተቋማት የሚመሩበት የፖሊሲና አዋጅ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ

309 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ልዩ (ሰበር) አንኳር ዜና || Konso News | Konso News Special (Breaking) News

November 02, 2022 18:42 - 6 minutes - 6.1 MB

የዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ላለፉት 10 ቀናት ሲደረግ የነበረው ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ

308 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 19, 2022 18:45 - 11 minutes - 10.9 MB

የዕለተ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. በሐዋሳ የሚኖሩ የኮንሶ ተወላጆች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 18 ኩንታል የበቆሎ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ 2. በኮንሶ ዞን የመጀመሪያው የአካል ጉዳተኞች ማበልጸጊያ ማህበር መቋቋሙ ተገለጸ 3. አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ከዛሬ ጀምሮ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ 4. የብሪታኒያ ንግስት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ የቀብር በዛሬው ዕለት በልዩ ክብር ተከናወነ

307 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 15, 2022 08:08 - 9 minutes - 9.15 MB

የዕለተ ሐሙስ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ 2. “አጫይላ” የተሰኘ የህጻናት የአፋ ኾንሶ ፕሮግራም ሥርጭት በFM 90.9 ሊጀመር ነው 3. የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተገለፀ 4. የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው ተባለ

306 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 14, 2022 08:59 - 11 minutes - 10.3 MB

የዕለተ ረቡዕ መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. “ኮንሶን እናስተዋውቅ” በሚል መሪ ሐሳብ በዘመን መለወጫ ቀን የተዘጋጀው የቁንጅናና ባህልን የማስተዋወቅ ውድድር በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ 2. በብልፅግና ጉባዔ፣ ዕጩ ተመራጭ አስመራጭ ሆኖ መሰየሙ ትክክል እንዳልነበር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ 3. ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈፀሙ

305 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 12, 2022 09:08 - 16 minutes - 15.4 MB

የዕለተ ሰኞ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. ሄስ ትራቭል ኢትዮጵያ በኮንሶ ዞን በ180 ሚሊዮን ብር የእንቨስትመንት ተቋማት እየገነባ ነው ተባለ 2. ህወሓት ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታወቀ 3. የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ 4. ኤምባሲዎች በግቢያቸው ስብሰባ ከማድረጋቸው በፊት ለመንግሥት እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተላለፈ

304 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 08, 2022 17:24 - 15 minutes - 14.2 MB

የዕለተ ሐሙስ ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ መከረ 2. ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ምንም ዓይነት ግብይት እንዳይደረግ ከለከለ 3. ሩሲያ፤ በቁጥጥሯ ስር ባሉ የዩክሬን ግዛቶች በመጪው ህዳር ወር “ህዝበ ውሳኔ” ልታካሂድ ነው 4. አፕል ኩባንያ በአደጋ ወቅት ኔትዎርክ ከሌለበት ስፍራ በሳታላይት አማካይነት መልዕት የሚልክ አይፎን 14 የተሰኘን  ይፋ አደረገ

303 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 07, 2022 18:12 - 11 minutes - 10.6 MB

የዕለተ ረቡዕ ጳጉሜ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን የሰው ሀብት ልማት ምጣኔ ለመጨመር የሚረዳ የመረጃ ቋት ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው 2. ‹‹ኢትዮጵያን የመበተን ዕቅድ በዚህኛው የጦርነት ምዕራፍ ይቋጫል›› ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን  ገለጹ 3. ቻይና በትንፋሽ የሚወሰድ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ይፋ አደረገች

302 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 05, 2022 16:17 - 17 minutes - 16.3 MB

የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. በካራት ከተማ ሲካሄድ የነበረው የኮንሶ የምሁራን የምክክር ጉባኤ ተጠናቀቀ 2. መንግሥት ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ 3. የኬንያ ፍ/ቤት የዊሊያም ሩቶ አሸናፊነትን አፀና 4. ሊዝ ትረስ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

301 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

September 01, 2022 17:44 - 12 minutes - 11.8 MB

የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. ሲጠበቅ የነበረው የኮንሶ ምሁራን አመታዊ የምክክር ጉባኤ ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገለጸ 2. በኮንሶ በኩል ወደ አርባምንጭ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 11 ኩንታል የቡና ምርት በቁጥጥር ሥር ዋለ 3. በኢትዮጵያ አየር ክልል ከተመታው አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የየትኛውንም ሀገር ስም አልተጠቀሰም ሲል በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ 4. ከ20 ሺህ በላይ በሆኑ ንቦች የተነደፈው አሜሪካዊ ከሳምንት በኋላ ነፍስ ዘራ 5. ፖላንድ ጀርመን በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ላደረሰችባት ጉዳት ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች

300 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

August 29, 2022 18:06 - 12 minutes - 11.9 MB

የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. የመብራት ኅያል ካራት ቅርጫፍ ጽ/ቤትና የካራት ማዘጋጃ ቤት ውዝግብ በውይይት መፈታቱ ተገለጸ 2. በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር ለምስክር ትፈለጋላችሁ የተባሉ አርብቶ አደሮች በእሥርና እንግልት መዳረጋቸው ተገለጸ 3. ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ 4. ሰሜን ኮሮያ ጠላትን ለማሳሳት በሚል ስምንት ተመሳሳይ ቤተ መንግስቶችን ገነባች

299 || ከእኛው ለእኛው የውይይት መርሃ ግብር || መጪው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ

August 27, 2022 18:18 - 2 hours - 207 MB

በዛሬው ውይይት፡  1) 2013 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የተደረገው የመጀመሪያው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ ምን ምን አዎንታዊ ውጤቶችን አስገኘ?  2) በአምናው የምክክር መድረክ የተቀመጡ ተግባራት ምን ምን ናቸው? የትኞቹስ ተሳኩ? የትኞቹስ አልተሳኩም?  3) ከነሐሴ 26 እስከ 28፣ 2014 ዓ.ም ሊካሄድ ባለው 2ኛው የኮንሶ ምሁራን ምክክር ላይ ምን ምን ሐሳቦችን እንጠብቅ?? የሚሉና ሌሎችም ሐሳቦች በውይይቱ ተንሸራሽረዋል። 

298 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

August 25, 2022 18:29 - 16 minutes - 15.6 MB

የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን 62 በኩፍኝ የተጠቁ ሰዎች መመዝገባቸውንና በሽታው ወረርሽን መሆኑን የዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ 2. የኮንሶ ዞን ምሁራን የምክክር መድረክ ከነሐሴ 26-28 እንደሚሆን ተገለጸ 3. የካራት ከተማ አስተዳደር ለዘመን መለወጫ በዓል ለከተማው ነዋሪዎች የሚሆን የአስቤዛ ባዛር ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታወቀ 4. ኢትዮጵያ ከአጎአ እድል በመታገዷ ምክንያት ከሀገር የተሰደደ ኩባንያ አለመኖሩ ተገለጸ 5. ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት 20 በመቶ ግዛቷን ማጣቷ ተገለጸ

297 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

August 24, 2022 17:35 - 10 minutes - 9.74 MB

የዕለተ ዕሮብ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን መንግሥት የሚከተለው አካሄድ በመጪው የምሁራን ስብሰባ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖረው የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ተገለጸ 2. የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ኃይል የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላንን መቶ መጣሉን አስታወቀ 3. የተመድ ዋና ፀሃፊአንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም በአስቸኳይ ወደነበረበት እንዲመለስ አሳሰቡ

296 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

August 22, 2022 17:01 - 12 minutes - 11.1 MB

የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት በ5ኛ መደበኛ ስብሰባው ወቅታዊው የድርቅ ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጉ ተገለጸ 2. መንግሥት ከሕወሓት ጋር የፖለቲካ ውይይት በማድረግ ቀሪ ጉዳዮችን በብሔራዊ ምክክሩ እንዲፈቱ እፈልጋለሁ አለ 3. ሶማሊያ የሽብር ጥቃትን ቀድመው ያልተከላከሉ የሥራ ኃላፊዎችን እንደምትጠይቅ ገለጸች

295 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest

August 18, 2022 18:04 - 12 minutes - 11.3 MB

የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 12  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት በዛሬው ውሎው የተለያዩ ልማት ነክና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ መምከሩ ተገለጸ 2. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ለ2015 ዓ.ም 700 ሚልዮን ብር ገደማ በጀት በማጽደቅ ማምሻውን ስብሰባውን አጠናቀቀ 3. በኢትዮጵያ 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ም/ቤት ወሰነ